Announcement የጥናትና ምርምር ፐብሊኬሽን የስራ ክፍል የሰራቸውን አራት ጥናታዊ ጽሑፎች አቀረበ።

የጥናትና ምርምር ፐብሊኬሽን የስራ ክፍል የሰራቸውን አራት ጥናታዊ ጽሑፎች አቀረበ።

26th July, 2025

ተግባረዕድ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን

ሀምሌ 15/2017/ዓ.ም

የአዲስ አበባ ተግባ-ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  ጥናትና ምርምር ፐብሊኬሽን የስራ ክፍል በ2017 በተለያዩ ርእሶች ላይ የሰራቸውን ጥናታዊ ጽሑፎች አጠቃላይ የAC እና ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት አቀረበ። 

በጥናታዊ ጽሁፎቹ የብልሹ አሰራር  ተጋላጭነት  የሚያሳይ የዳሠሳ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በሌላ ጥናታዊ ጽሑፍ የኮሌጃችን የትብብር ስልጠና ትግበራ ምን እንደሚመስል የተገኙ ግኝቶች ቀርበዋል። አጠቃላይ የውስጥ እና የውጭ ተገልጋዮች እርካታ ላይ የተሰራው የዳሰሳ ጥናት ሌላኛው በእለቱ የቀረበ ጥናታዊ ጽሑፍ ሲሆን በጥናቱም የውስጥ እና የውጭ እርካታ ያለበትን ደረጃ መለየት ተችሏል።

በመጨረሻም ከስራ ትስስር አንጻር የኮሌጁን አፈጻጸም ለመለካት የተሰራው የትሬሰር ስተዲ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የነዚህ ጥናታዊ ጽሑፎች ዋና ዓላማው በኮሌጁ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ስኬት እና ያሉ ክፍተቶችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ በጥናት መለየት፣ እልባት ለመስጠት እና የስልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው ተብሏል ።

በአጠቃላይ የጥናቱ ሂደት እንዴት  የአሠራር ሥርዓቶችን  ተከትሎ እንደተሠራ፣ የተገኙ ዋና ዋና ግኝቶች እና የመፍትሄ ሀሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። 

የኮሌጃችን ዋና ዲን አቶ ተስፋየ አድማሱ ችግሩን ለመቅረፍ ሁሉም የስራ ክፍሎች  የጥናቶቹን ግኝቶች የእቅድ አካል በማድረግ የስራችንን ውጤታማነት ማረጋገጥ አለብን ብለዋል ።

ተግባረዕድ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን

.

Copyright © All rights reserved.

Created with