Call us:
+115517329
|
Mail us for help:
tegbareidpolytech@aatvetb.edu.et
|
Help center
360° Support - We are here to assist you.
A.ATegbare'id PolyTechnic College
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
User Manual
Application Form
Registration Form
Status
More
News
User Manual
Login
User Manual
የኢንኩቤሽን አገልግሎቱን በአዲሱ የዘርፉ እሳቤ ተቃኝቶ መተግበር እንደሚገባ ተገለፀ።
የኢንኩቤሽን አገልግሎቱን በአዲሱ የዘርፉ እሳቤ ተቃኝቶ መተግበር እንደሚገባ ተገለፀ።
22nd February, 2025
የኢንኩቤሽን አገልግሎቱን በአዲሱ የዘርፉ እሳቤ ተቃኝቶ መተግበር እንደሚገባ ተገለፀ።
የካቲት 14/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝ እና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እና ኢንኩቤሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በኢንኩቤሽን አገልግሎት፤ በዞኒንግ እና ዲፈረሸንሼን ዙሪያ ለኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ዲኖች እና አስተባባሪዎች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት በኢንተርፕራይዝ እና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እና ኢንኩቤሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጸጋዬ በየነ ስልጠናው በዘርፉ የሚሰጠውን የኢንኩቤሽን አገልግሎት በአዲሱ የዘርፉ እሳቤ ተቃኝቶ አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦችን በማከል ወደ ገበያ እንዲገቡ ያስችላል ብለዋል።
አሁን ላይ የኢንኩቤሽን አገልግሎቱ በተወሰኑ ኮሌጆች የተጀመረ መሆኑን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ ስራው በሁሉም ኮሌጆች ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማድረግ ሂደት ስልጠናው ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰዋል።
ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በሚካሄደው ስልጠና በኢንኩቤሽን ምንነትና አተገባበር ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ነባራዊ ሁኔታ ጋር ባገናዘበ መልኩ ግንዛቤ እንደሚፈጠር እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ይጠበቃል።
.