Announcement '' የተቋም ውስጥ ምዘና መስጠት ተጀመረ ::''

'' የተቋም ውስጥ ምዘና መስጠት ተጀመረ ::''

10th July, 2025

ሀምሌ 2/2017/ዓ.ም

የአዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በስራና ክህሎት ቢሮ የተዘጋጀውን የተቋም ውስጥ ምዘና መስጠት ጀመረ ።

በስራና ክህሎት ቢሮ አስተባባሪነት ከተለያዩ ኮሌጆች በተውጣጡ አሰልጣኞች የተዘጋጀው የተቋም ውስጥ ምዘና የ10ሩም ስልጠና ዘረፎች ተመራቂ ሰልጣኞች በአዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እየተፈተኑ ይገኛሉ ።

የምዘና ዋና አላማ ሰልጣኞች ወደ ብሔራዊ ምዘና ከመሄዳቸው በፊት ያላቸውን ክፍተት ለመለየት እና ያለፉትም የብሔራዊ ምዘናን ለምዘናው  ያላቸውን ዝግጁነት ለማወቅ ነው። 

ምዘናውን ያላለፉ ሰልጣኞች skill gap ተለይቶ ድጋፍ ተደርጎላቸው መብቃታቸው ሲረጋገጥ ወደ ብሔራዊ የብቃት ምዘና ማእከል እንደሚላኩ የስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን የሆኑት አቶ ደረሰ ጌታቸው ገልጸዋል።

ተግባረዕድ ኮሚዩኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት

.

Copyright © All rights reserved.

Created with