Announcement ሳምንታዊ  የወርቃማ ሰኞ  /የአብሮነት/ጊዜ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ።

ሳምንታዊ  የወርቃማ ሰኞ  /የአብሮነት/ጊዜ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ።

19th August, 2025

የአዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በጉጉት የምንጠብቀው   አስተማሪ የሆነ ሳምንታዊ የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር አካሄደ ።

ኮሌጁ በየሳምንቱ የሚያካሂደው የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር   ''ወርቃማ ሰኞ ለወርቃማ ሳምንት'' በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት ከአጠቃላይ የኮሌጁ ማህበረሰብ በተገኘበት ተካሂዷል ። 

የአዲስ አበባ  ተግባረእድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኢንኩቬሽን ማዕከል አስተባባሪ አቶ ዳዊት ሀጎስ  why from idea to action  /weekly /plan    በሚል ርዕስ ለኮሌጁ ማህበረሰብ በሰነድ   አቅርበዋል ። 

ሀሳብ በተግባር ካልታገዘ  ምንም ዋጋ እንደሌለው አሳስበዋል። አንድን አምነንበት የምንሰራው ስራ  ሀሳብ ወደ ተግባር  ለመለወጥና ስኬታማ ስራ ለመስራት በእቅድ መመራት አለብንብለዋል ። በዚህ ሳምንት ምን ሰራን  ብለን ለራሳችን መጠየቅ አለብን ብለዋል።

በመጨረሻም   ሁሌም ሰኞ ሰኞ ከስራ ሰአት በፊት የአብሮነት መድረክ መኖሩ የሚበረታታ በመሆኑ የኮሌጁ ማህበረሰብም በዚሁ እንዲቀጥል አስተያየት ሰጥተው መርሀ ግብሩ ተጠናቋል ።

ተግባረዕድ ኮሚዩኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት

.

Copyright © All rights reserved.

Created with