Announcement የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ወርክሾፕ/Action Research Work Shop / ለኮሌጅ የAC አባላት ግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ

የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ወርክሾፕ/Action Research Work Shop / ለኮሌጅ የAC አባላት ግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ

18th January, 2026

በአዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት የጥናት ምርምር ክፍል ከሌሎች ክፍሎች በጋራ የሚያከናውነው የጥናት ስራን በላቀ አፈፃፀም ለማጠናቀቅና ተቀራራቢ  ግንዛቤ ለመፍጠር ታልሞ የተዘጋጀ ወርክ ሾፕ ነው ።

በግንዛቤ ማስጨበጫውም በአቶ በለጠ ቢራቱ "Driving Innovation and Excellence at AATPTC በሚል ርዕስ በሰነድ አቅርበዋል ።

የጥናት ስራዎችን ለመምራት የስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎችና አስተባባሪዎች የሚኖራቸውን ሚና  የስራ ድርሻ ላይ በማተኮር የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል ።

በቀርበዉ ሰነድ ላይ ተሳታፊዎች የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ግንዛቤ ማሰጨበጫው ለስራችን በቂ ዕውቀትን ያስጨብጠናል እና በትብብር እንደምንሰራ ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል ።  ተሳታፊዎችም አክለውም ይህን ግንዛቤ ለአሰልጣኞች ቢሰጥ ለጥናት ስራችን በጣም ይጠቅመናል ሲሉ ገልፀዋል ።

በመጨረሻም የቴክኖሎጂ ልማትና የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት  ም/ዲን አቶ መሀመድ ጠይብ እንደገለፁት  Action Research  አዳዲስ አሰራርና ፈጠራ ልምዶችን ለማሳደግ የተቋሙን አፈጻጸም ላይ አወንታዊ ተፅዕኖ ስለማፈጥር በጣም ትኩረት መስጠት እና በቁረጠኝነት ከሰራን ከባለፈዉ  ዓመት የተሻለ ውጤት ማምጣት  እንችላለን በማለት የስራ አቅጣጫ በመስጠት መርሀ ግብሩ ተጠናቋል ።

ተግባረዕድ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ህዳር 19/2018 ዓ.ም

.

Copyright © All rights reserved.

Created with